ቃለ መጠይቅ ላደረጉ ጥገኝነት ጠያቂዎች ተጨማሪ መረጃ
የፊንላንድ የስደተኞች አገልግሎት ከቃለ መጠይቅ በኋላ ተጨማሪ ማብራሪያ ሊጠይቅዎት ይችላል። መልስዎን በተሰጠው የጊዜ ገደብ ዉስጥ ይላኩ።
የኢሚግሬሽን ጽሕፈት ቤት ከቃለ መጠይቁ በኋላ ማመልከቻዎን ማየቱን ይቀጥላል። ተጨማሪ መረጃ ከእርስዎ የምንፈልግ ከሆነ ለተጨማሪ ማብራሪያ ጥያቄ ልንልክልዎ ወይም የቋንቋ ፈተና ልንሰጥዎ ወይም ለሌላ ምርመራ ልንጠራዎ እንችላለን።
ተጨማሪ ማብራሪያዎች
- ተጨማሪ የጽሁፍ ማብራሪያ ከእርስዎ የምንፈልግ ከሆነ የተጨማሪ ማብራሪያ ጥያቄ ደብዳቤ እንልክልዎታለን። የመልስዎ ኢሚግሬሽን ጽ/ቤት የመድረሻ ጊዜ ገደብ መቸ እንደሆነ በደብዳቤው እንነግርዎታለን።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ ጥያቄው የጊዜ ገደቡ ሳያልፍ መልስ ይስጡ። የመልስዎ የጊዜ ገደቡ ካለፈ በኋላ የፊንላንድ የስደተኞች አገልግሎት ከደረሰ ኃላፊነቱ የእርስዎ ነው። ሆኖም ግን ለተጨማሪ መረጃ ጥያቄ መልስ ባይሰጡም የፊንላንድ የስደተኞች አገልግሎት በማመልከቻዎ ላይ ላይ ብቻ ተመርኩዞ ውሳኔ ሊሰጥ
- የህግ ረዳት ካሎት፣ እሱ ወይም እሷ መልሱን ወደ ኢሚግሬሽን ቢሮ መላክ ይችላሉ። ስለዚ ህ ጉዳይ ረዳትዎን ያነጋግሩ።
አዲስ ቃለ፡ምልልስ
- ለአዲስ ቃለ፡ምልልስ ከጠራንዎት፣ መቀበያ ማእከሉ ጥሪውን ያሳውቅዎታል። በድጋሚ ለምን ከእርስዎ መስማት እንደምንፈልግ በጥሪው ደብዳቤ ውስጥ እናሳውቆታለን።
- ለአዲሱ ቃለ ምልልስ ከመቀረብዎ በፊት የጥሪውን ደብዳቤ እና በውስጡ ያሉትን መመሪያዎች በጥንቃቄ ያንብቡ።
- በሰዓቱ ይገኙ። ያለ በቂ ምክንያት ጥሪውን ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍ አይችሉም። ያለ በቂ ምክንያት በጥሪው ላይ ካልተገኙ፣ አዲስ ጥሪ ሳይደረግ በማመልከቻዎ ላይ ውሳኔ መስጠት እንችላለን።
ከቃለ መጠይቁ በኋላ ተጨማሪ ማብራሪያዎችን እራስዎ መላክ ይችላሉ።
ሁኔታዎ ላይ ለውጥ ከመጣ ወይም ለማመልከቻዎ ድጋፍ ሌላ ተጨማሪ መረጃ ካገኙ ከቃለ መጠይቁ በኋላም ተጨማሪ መረጃዎችን፣ ማለትም እንደ የህክምና ምስክር ወረቀት፣ የመታወቂያ ሰነድዎን፣ ወይም ወደ ኢሚግሬሽን ጽ/ቤት ያላስገቡትን ተጨማሪ መረጃ ወደ ኢሚግሬሽን ቢሮ መላክ ይችላሉ። እባክዎ መግለጫውን በተቻለ ፍጥነት ይላኩ። የሕግ አማካሪ ካሎት፣ ይህንን ጉዳይ ከእሷ/ከእሱ ጋር ይወያዩ።
ማመልከቻዎ እየታዬ ባለበት ወቅት አድራሻዎ፣ የስልክ ቁጥርዎ ወይም የኢሜል አድራሻዎ ከተቀየረ ለውጦቹን ለቅበላ ማእከሉ ወዲያውኑ ያሳውቁ።
ለጥገኝነት ጠያቄ ማመልከቻዎ ተጨማሪ ማብራሪያዎችን በሚከተለው መንገድ ይልካሉ።
ተጨማሪ መረጃውን በኢሜል ወይም በደብዳቤ ይላኩ። ተጨማሪ መግለጫውን ወደ የአገልግሎት ጽ፨ቤታችን ማምጣትም ይችላሉ። በተጨማሪ መግለጫው ውስጥ የባለጉዳይ ቁጥርዎን እና የማህደር ቁጥርዎን ይጻፉ። ለምሳሌ የባለጉዳይ ቁጥርዎን እና የማህደር ቁጥርዎን በቃለ መጠይቁ ጽሁፍ ወይም ተጨማሪ ማብራሪያ መጠየቅያ ደብዳቤ ገጽ የላይኛው ቀኝ ጥግ ላይ ሊያገኙት ይችላሉ።
ዋናውን ሰነድ ወደ ፊንላንድ የስደተኞች አገልግሎት እንዲልኩ ጠይቀኖት ከሆነ ሰነዱን በተመዘገበ ደብዳቤ መላክ አለቦት። የተመዘገበ ደብዳቤ አላላክን ከቅበላ ማዕከልዎ ወይም ከህግ ረዳትዎ ምክር መጠየቅ ይችላሉ። ከፈለጉ ኦርጅናል ሰነዶችን ወደ የአገልግሎት ጽ/ቤታችን ማምጣት ይችላሉ።
ኢ - ሜይል (የኤልክትሮኒክስ መልዕክት)
ተጨማሪ ማብራሪያዎን migri@migri.fi. በሚል አድራሻ በኢ - ሜይል (የኤልክትሮኒክስ መልዕክት) ይላኩ። በኢ - ሜይል (የኤልክትሮኒክስ መልዕክት) ሲልኩ የኢሚግሬሽን ጽሕፈት ቤት አድራሻን ወይም - Securemail-service (securemail.migri.fi) - ይጠቀሙ። ሰኪውር ሜል አገልግሎት መልዕክቶችዎን በሚስጥር ያስተናግዳል። ኢሚግሬሽን ጽሕፈት ቤት ከራሱ ሰኪውር ሜል አገልግሎት ውጪ ሌሎች ሰኪውር መልእክቶችን መክፈት አይቻለውም። የሰኪውር ሜል አገልግሎት አጠቃቀም መመሪያዎችን ከአገልግሎት ጽህፈት ቤቱ ድረ-ገጽ ላይ፣ “Contact information“ ርዕስ ስር፣ ያንብቡ።
የፖስታ አድራሻ
ተጨማሪ ማብራሪያውን በፖስታ የሚልኩ ከሆነ ደብዳቤውን ወደ በኢሚግሬሽን ቢሮ አድራሻ፣ ፖስታ ሳጥን ቁጥር 10፣ 00086፣ ሄልሲንኪ ይላኩ።
መልስዎን ወደ አገልግሎት ጣቢያችን ማምጣትም ይችላሉ።
ቀጠሮ መያዝም ሆነ የወረፋ ቁጥር መውሰድ አያስፈልግዎትም። ተጨማሪ ማብራሪያውን በአገልግሎት መስጫ ጣብያው አዳራሽ ባለው የፖስታ ሳጥን ውስጥ ያስቀምጡት። የአገልግሎት ጣብያውን ክፍት የመሆኛ እና የመገናኛ ሰዓቶችን በአገልግሎት ጽህፈት ቤቱ ድረ-ገጽ ላይ፣ Service points ርዕስ ስር፣ ይመልከቱ።
በፈቃደኝነት ስለመመለስና ስለሚደረግለት ዕገዛ
ወደ ትውልድ ሀገርዎ ወይም የመኖር መብት ወዳለዎት ሀገር መመለስ ከፈለጉ በፈቃደኝነት የመመለሻ ድጋፍ ለማግኘት ማመልከት ይችላሉ። ድጋፍ ለመስጠት አንዳንድ መሙዋላት ያለባቸው ሁኔታዎች ስለአሉ ለድጋፍ ሲያመለክቱ ሁኔታዎቹ ይጣራሉ። ለታገዘ በፈቃደኝነት መመለስ ማመልከት ከፈለጉ የመቀበያ ማእከሉን ሰራተኛ ያነጋግሩ። የእንግዳ መቀበያ ማእከሉ በፈቃደኝነት የመመለስ ማመልከቻን እንዴት እንደሚያቀርቡ ይረዳዎታል፤ በማመልከቻዎ ላይም ውሳኔ ይሰጣል። ይረዳዎታል።
የታገዘ በፈቃደኝነት መመለስ ማለት ወደ ሀገርዎ መመለስ የሚያስችሎት ድጋፍ እና እርዳታ ማለት ሲሆን፤
- በጥገኝነት ጥየቃ ማመልከቻዎ ላይ አሉታዊ ውሳኔ ደርሶዎታል
- የጥገኝነት ጥየቃ ማመልከቻዎን መሰረዝ ይፈልጋሉ
- ለእርስዎ የተሰጠው የዓለም አቀፍ ጥበቃ ሁኔታ ተቋርጧል ወይም
- እርስዎ የሰዎች ዝውውር ሰለባ ነዎት።
ለመመለሻዎ የተለያዩ ድጋፎችን ማግኘት ይችላሉ፡ ምን ዓይነት ድጋፍ ማግኘት እንደሚችሉ እዚህ ያንብቡ
የታገዘ በፈቃደኝነት መመለስ ድጋፍ የሚያጠቃልለው የጉዞ ዝግጅቶችን፣ የአየር ማረፊያ ላይ ዕገዛን እና የተመጠነ የገንዘብ ድጋፍን ነው። ይህም ወደ አገርዎ ከተመለሱ በኋላ በተመለሱበት ሀገር ውስጥ በሚሠራ ድርጅት የሚከፈል ይሆናል።
ዐይ-ኦ-ኤም (IOM) ወይም አለምአቀፍ የስደተኞች ድርጅት ለታገዘ በፈቃደኝነት መመለስ የጉዞ ዝግጅቶች ሃላፊነትን ይወስዳል። አስፈላጊ ከሆነ፣ ዐይ-ኦ-ኤም (IOM) ከአገርዎ ኤምባሲ የጉዞ ሰነድ እንድታገኙ እና በፊንላንድ የተወለዱ ልጆቻችሁን በዜግነት ተመዝግበው እንዲመለሱ ያግዝዎታል። የጤና ችግሮች ካጋጠሙዎት፣ ዐይ-ኦ-ኤም (IOM) በመመለሻ ዝግጅቶች ግምት ውስጥ ያስገባቸዋል።
በታገዘ ፈቃደኝነት መመለስ ማመልከቻዎ ላይ ውሳኔ ሲደርስዎ፣ ምን ዓይነት እርዳታ ሊያገኙ እንደሚችሉ በውሳኔው ውስጥ መረጃ ያገኛሉ። ዕገዛው በዋነኝነት የሚሰጠው በቁሳቁስ መልክ ነው። ይህ ማለት እርስዎን የሚያግዙ የተለያዩ አገልግሎቶች ወይም አቅርቦቶች ለምሳሌ የራስዎን ንግድ ለመጀመር የሚረዳዎ፣ ስልጠና ወይም ጥናት፣ የኑሮ ወጪዎች ወይም የጤና እንክብካቤ ወጪዎች።
የታገዘ በፈቃደኝነት የመመለስ ቅድመ ሁኔታ በራስዎ ፈቃድ ከፊንላንድ ለመሄድ መወሰንዎ ነው። በመጠባበቅ ላይ ያሉትን የጥገኝነት፣ የመኖሪያ ፍቃድ ወይም የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ጥየቃ ማመልከቻዎችን ሁሉ እና ይግባኞችን መሰረዝ አለቦት።
በፈቃደኝነት ስለ መመለስ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ የራስዎን ቅበላ ማእከል ወይም የፊንላንድ የስደት አገልግሎትን ይጠይቁ
በእንግዳ መቀበያ ማእከል ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ የእራስዎን መቀበያ ማእከል ሰራተኛ ያነጋግሩ። በእንግዳ መቀበያው ውስጥ የማይኖሩ ከሆነ፣ የፊንላንድ የስደተኞች አገልግሎትን ያነጋግሩ፡፡
- የስልክ ቁጥር 050 413 8625 (እንዲሁም WhatsApp)።
- የኢሚግሬሽን ጽሕፈት ቤት የደኅንነት መልእክት አገልግሎት - Securemail-service (securemail.migri.fi) - በኩል፣ return@migri.fi አድራሻ በመጠቀም ኢ-ሜል ቢልኩ የመልዕክቱ ሚስጥርነት እንደተጠበቀ ይደርሳል።
ተጨማሪ ንባብ
በፈቃደኝነት መመለስ --- Voluntary return
ሌሎች የመኖሪያ ፈቃዶች
ስለ ሌሎች የመኖሪያ ፈቃዶች እና መሠረታቸውን በተመለከተ መረጃዉን በድረ፡ገጹ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
- የመኖሪያ ፈቃድ ጥያቄ ማመልከቻ --- Applying for a residence permit
- የመጀመሪያ የመኖሪያ ፈቃድ --- First residence permit
ማመልከቻዎች ያስከፍላሉ።